Skip to main content

Popular posts from this blog

photo pad

እቴ ይስጥሽ

እቴ ይስጥሽ ከቁመቴ ከላዬ ቀንሶ ያስረዝምሽ አንቺን እኔን አሳንሶ ከሰጎን እረዝመሽ ስትቆሚ ከጎኔ ቁመቴን መጽውቼሽ ጫጩት ላክል እኔ፤ ይስጥሽ ከጸጉሬ ከአናቴ ላይ ዘግኖ ይገጠብ ራሴ ያንቺ ተጎንጉኖ አወይ ጸጉሯ ብለው ኮረዶችሲያወሩ ድጥ ራስ ነህ ብሎ ይዝለፈኝ ሰፈሩ፤ እቴ ይስጥሽ ከወዜ ላይ ጨልፎ ከፊቴ ይቅዳልሽ ከደሜ ጠልቆ ከጅማቴ ከአይን ያውጣሽ እያለ ሲመርቅ አድናቂ እስቲ እግዜር ይማርህ ይበለኝ ጠያቂ። እቴ እጄን ብትፈልጊ እግሬን ብትፈልጊ አንገቴን ደረቴን ተሰጥኦ ሀሳቤን ያደምቀኛል ብለሽ ያሰብሺውንሁላ እግዜር ከኔ ወስዶ ከሰጠሽ በኋላ ያስቀርልኝ አይኔን አንቺን ማየት ብቻ ያኖረኛል እኔን። በእውቀቱ ስዩም