Skip to main content

እቴ ይስጥሽ

እቴ
ይስጥሽ ከቁመቴ ከላዬ ቀንሶ
ያስረዝምሽ አንቺን እኔን አሳንሶ
ከሰጎን እረዝመሽ ስትቆሚ ከጎኔ
ቁመቴን መጽውቼሽ ጫጩት ላክል እኔ፤
ይስጥሽ ከጸጉሬ ከአናቴ ላይ ዘግኖ
ይገጠብ ራሴ ያንቺ ተጎንጉኖ
አወይ ጸጉሯ ብለው ኮረዶችሲያወሩ
ድጥ ራስ ነህ ብሎ ይዝለፈኝ ሰፈሩ፤
እቴ
ይስጥሽ ከወዜ ላይ ጨልፎ ከፊቴ
ይቅዳልሽ ከደሜ ጠልቆ ከጅማቴ
ከአይን ያውጣሽ እያለ ሲመርቅ አድናቂ
እስቲ እግዜር ይማርህ ይበለኝ ጠያቂ።
እቴ
እጄን ብትፈልጊ
እግሬን ብትፈልጊ
አንገቴን ደረቴን
ተሰጥኦ ሀሳቤን
ያደምቀኛል ብለሽ ያሰብሺውንሁላ
እግዜር ከኔ ወስዶ ከሰጠሽ በኋላ
ያስቀርልኝ አይኔን
አንቺን ማየት ብቻ ያኖረኛል እኔን።
በእውቀቱ ስዩም

Comments

Popular posts from this blog

የኢትዮ ቆንጆ

photo pad

COMPUTER MANUAL BY AMHARIC

  BASIC COMPUTER MANUAL   A. Unit One:- introduction    What is computer?    A computer is an electronic device that manipulates information, or data.   It has the ability to store, retrieve, and process data. You may already know that you can use a computer to type documents, send email, play games, and browse the Web.  You can also use it to edit or create spreadsheets, presentations, and even videos.  ኮምፒተር ምንድን ነው?  ኮ ምፒውተር ማለት መረጃን የሚጠቀም ኤሌክትሮኒክ መሣሪያ ነው  መረጃን የማከማቸት ፣ የማምጣት እና የማካሄድ ችሎታ አለው።  ሰነዶችን ለመተየብ(ለመፃፍ) ፣ ኢሜል ለመላክ ፣ ጌሞችን እና ጨዋታዎችን ለመጫወት እና እንዲሁመ ድህረገፆችን ለማሰስ ኮምፒተርን መጠቀም እንደሚችሉ አስቀድመው ያውቁ ይሆናል።  እንዲሁም የተመን ወይም ሂሳብ ስራወችን ለመስራት ፣ዉስብስብ ና ብዛት ላቸዉን መረጃወች ለመተንተን ፣ ቪዲዮዎችን ና ድምፆችን ለማየት ለመስማት እንዲሁም ለማዘጋጀት ፣ ለመፍጠር ሊጠቀሙበት ይችላሉ። 2.  የኮመፒዩተር ትዉልድ (COMPUTER GENERATION)  1.  FIRST GENERATION: VACUUM TUBES (1940-1956)   The first computer systems used vacuum tubes for circuitry and magnetic drums f...